ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እንዴት ታውቃላችሁ?

የቤት እና የቤተሰብ ለድንገተኛ ሁኔታ የሚያስፈልጉ ይዝግጅት መመሪያዎች

ውድ ነዋሪዎች:

ለተፈጥሮ አደጋ ወይም ለድንገተኛ ሁኔታዎች በእርግጥ ዝግጁ ነን?

የሃይፋ ከተማ ባለፉት አስር ዓመታት እውነተኛ ለውጥ እያለፈች እና በዚህ መስክ ውስጥ የመሪነት ደረጃ አላት:: በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ብዙ እውቀት እና ልምድ ሸምተናል:: ለናንተ ቤቶች እና ቤተሰቦች ለማዘጋጀት ይረዳቸዋል በማለት በዚህች መጽሔት ያሰፈርነውን የልምድ ምክር ከእናንተ ጋር ለማጋራት በማሰብ ነው:: ከእኛ ከነዋሪዎች የሚጠበቀው ልምድ እና ቅድመ ዝግጅት ፀጥታ ኃይሎችን ወይም የመንግሥት የማዘጋጃ ቤት ሥርዓት ለመተካት አለመሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ነው::

ይሁን እንጂ ከነዋሪዎች ጋር የጥምር ስራ በተለይ በድንገተኛ ወቅት በጣም ጥሩ ውጤት ሊያመጣ የሚችል ነው:: ልክ የሃይፋ ማዘጋጃ ቤት ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን ሁል ጊዜ እንደ ሚደረገው ልምምድ: እኛ ነዋሪዎችም የመማር እና የመዘጋጀት ኃላፊነት አለብን::

እኔ ለሁላችን ሰላማ ቀናት እየተመኘሁ ክፉ አያድርስብን እላለሁ:: የእናንተው ዮና ያሃብ የከተማው ከንቲባ

ምን ማድረግ እንዳለባችሁ የሚረዱ 5 ምክረ ነጥቦች

1. "ሐይፋ በእጣት ንኪት" የተሰኘውን አፕሊኬሽን መተግበሪያ ያውርዱ::

ለድንገተኛ መመሪያዎች ለማግኘት (በሞባይል push)

2. መሰረታዊ የሆኑ ምግቦችን አዘጋጁ:

2-3 የሚሆኑ የሚኒራል የታሸገ ውኃ: የታሸገ ደረቅ ማብሰል የማይጠይቅ ምግብ: (የታሸጉ የተለያዩ ምርቶችን: የሕፃናት ምግብ)

3. ለድንገተኛ የኤሌክሪትሪክ ኃይል መቋረጥ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን አዘጋጁ:

  • የተሞላ ለድንገተኛ ጊዜ መብራት
  • የእጅ ባትሪ ከተጨማሪ የባትሪ ድንጋይ ጋር
  • የብዙኃን መገናኛ ትራንዚስተር ሬዲዮ ከነባትሪው (ከትርፍ ባትሪዎች ጋር) የሚዲያ ዘዴዎች ቴሌቪዥን: ኮምፒውተር ወዘተ::
  • የሞባይል ስልክ ከተንቀሳቃሽ ባትሪ መሙያ እና መጠባበቂያ ባትሪ
  • መድሃኒቶች እና የመጀመሪያ እርዳታ መለገሻ
  • መደበኛ ትቅል ናይለን (የተሰነጣጠቁ መስኮቶችን ማተሚያ)
  • የግል እና የጋራ የደህንነት መጠለያዎች ክፍሎችን (ሚቅላጥ/ማማድ) በጥሩ ሁኔታ ማዘጋጀት

4. ለምድር መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጣሚ አስፈላጊ መሳሪያዎችን አዘጋጁ:

  • ለበርካታ ቀናት የሚሆን የግል ቁሳቁሶችን በከረጢት ማዘጋጀት
  • የቤተሰብ እና የድንገተኛ ድርጅቶች ስልኮች ዝርዝር ማዘጋጀት
  • የህክምና ሰነዶችን እና የመታወቂያ ካርድ ኮፒ ማዘጋጀት

5. በድንገተኛ ጊዜ አንድ የበራ ሞባይል ስልክ ብቻ አስቀሩ::

የሌሎች የስልክ ባትሪዎች የረዥም ጊዜ የመብራት መቋረጥ አጋጣሚ ያገለግሉዋችኋል:: የሞባይል ባትሪዎችን ሰባስቡ ለአስፈላጊ ጊዜ ይሆናሉ::

ቤትን እና ቤተሰብን ለድንገተኛ ሁኔታዎች አዘጋጁ

ቤተሰባችሁ በሙሉ የደህንነት መጠለያዎችን እና (ሜርሃቭ ሙጋን) የማምለጫ መስመሮች ማወቃቸውን ያረጋግጡ::

አስቀድመው ከድርጊቱ ቦታ ውጭ የመገናኛ ቦታ እና የቤተሰብ ተወካይ ይምረጡ

የመጀመሪያ እርዳታ ጥናት አጥንታችሁ በቤታችሁ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ መሳሪያ ይያዙ

የቤተሰብ ለድንገተኛ ወቅት የሚሆኑ ማህደረ ቁሳቁሶችን እንደሚከተለው ያዘጋጁ:

  • የመገናኛ ዘዴወች: ሬዲዮ ከባትሪ ጋር/ ቴሌቪዥን/ ኮምፒዩተር ከኢንተነት ጋር
  • የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ እና መድሃኒቶች
  • የክሬዲት ካርድ መረጃ + የጥሬ ገንዘብ
  • የቤት እና የመኪና ትርፍ ቁልፎች
  • የታተሙ የምግብ ጣሳዎችን መክፈቻ
  • ፊሽካ (የእርዳታ መጥሪያ የሚያገለግል)
  • የእጅ ባትሪ እና ባትሪዎች / ለድንገተኛ ወቅት መብራት
  • ሻማ እና ክብሪት / ሲጋራ ማቃጠያ
  • የሞባይል ስልክ ከነመሙያው
  • ስሜታዊ ትርጉም ያለው ተፈላጊ ቁሳቁስ
  • የታሸገ ምግብ እንደ ተታተሙ ጣሳዎች የሚቆረጠሙ ዓይነት
  • ውሃ - ለአንድ ሰው 4 ሊትር ውሃ ለአንድ ቀን (ለ 3 ቀናት የሚሆን)
  • አስፈላጊ ሰነዶች(ኮፒ አድርጎ ከቤት ውጭ ማስቀመጥናዲጂታል ሚዲያ ጨምሮ)
    • የኩፓት ሆሊም ካርድ
    • የመታወቂያ ካርዶች የመንጃ ፈቃድ ጨምሮ
    • የመድኃኒት መግዣ ፈቃድ ሰነዶች
    • አስፈላጊ የስልክ ቁጥሮች ዝርዝር
አስታውስ! ከእናንተ አንዱ መሣሪያዎችን በየወቅቱ በየ ሦስት ወር የሚፈትሽ ሃላፊ አድርጉ (ውኃውን መቀየር ያለውን የምግብ ብቃት እና የዕቃዎችን ደህንነት በመመሪያው መሰረት)
ቤትን መልቀቅ የሚያስገድድ ሁኔታ ከሆነ: የቤቱን ቁልፍ በፀጥታ ኃይሎች እጅ ማቆየት ይመረጣል (የሠፈር በአደጋ ጊዜ ሠራተኞችና / የማህበረሰብ ፖሊሲ)

በተጨማሪ: ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አንድ ትንሽ ሻንጣ መውሰድ ይመረጣል::

  • ልብስ + የውስጥ ልብሶች
  • ጫማ
  • የመጸዳጃ ቁሳቁሶች
  • ቢላዋ ለተለያዩ ጥቅሞች

ስለ ቤተሰብዎ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች ያስቡ:

  • መሣሪያዎች እና የሕፃናት ምግብ
  • ጨዋታዎች እና ጋዜጦች
  • መጽሐፍት እና መጫወቻዎች

ከቤት ከመሄድ በፊት:

  • የኤሌክትሪክ ምንጮችን ማጥፋት
  • ጋዝን ቧንቧዎች መዝጋት
  • የውኃ ቧንቧዎችን መዝጋት
  • ቤትን መቆለፍ

የሚያስፈልግዎ መተግበሪያ (አፕሊቃጺያ)

አስፈላጊ መመሪያዎችንና ዝማኔዎችን ለማግኘት በመተግበሪያ (አፕሊቃጺያ) ብቸኛ መንገድ ሳይሆን አይቀርም "ሐይፋ በእጣት ንኪት"

ለማውረድ:

የተጠበቀ መጠለያ ቦታን ማዘጋጀት

የቤት/ፎቅ የተጠበቀ መጠለያ ቦታዎች የሚያስፈልጉ እቃዎች

  • የመገናኛ ዘዴወች: ሬዲዮ ከባትሪ ጋር/ ቴሌቪዥን/ ኮምፒዩተር ከኢንተነት ጋር
  • የእጅ ባትሪ እና ባትሪዎች / ለድንገተኛ ወቅት መብራት
  • የእሳት ማጥፊያ
  • ጊዜን የሚያሳልፉ እና የሚያዝናኑ ነገሮችን እንደ ጋዜጣና ጨዋታዎች
  • መደበኛ ትቅል ናይለን የተሰነጣጠቁ መስኮቶችን ማተሚያ
  • የቤተሰብ የአደጋ ጊዜ ስብስብ አቃዎች (ላይ ተመልከቱ)

የጋራ መጠለያ - የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች:

  • የሚሰራ መብራት የድንገተኛ መብራት ጨምሮ
  • ተገቢ መጸዳጃ ክፍል: የቧንቧ ውኃ እንዲሁም ተገቢ የውኃ ማጠራቀሚያ
  • ከትርፍ ቀቃዎች ነጻ
  • የመቀመጫ ቦታዎች

የመጠለያውን መሸሸጊያ ቦታ ማዘጋጀት እና መቆጣጠር:

በቤቶች ኮሚቲ አባል ሃላፊነት መጠለያው በሁሉም ወቅት ከአደጋ መሸሸጊያ ጥቅም እንዲውል የመንከባከብና የመጠበቅ ሐላፊነቱ: የጋራ ከሆነ የነዋሪዎች: በሃይፋ ከተማ ሃላፊነት- የህዝብ መጠለያዎችን የመጠበቅና የመጠገን ኃላፊነቱ የማዘጋጃ ቤት ባስፈለገ ደረጃ ደግሞ የሃይፋ ከተማ መጠለያዎች ዝግጁነት ያስከብራል
በሕጉ መሰረት"መጠለያ አያያዝ" ባለ መጠለያ ሰው በሙሉ መጠለያው ደረጃውን የያዘ ንጽህና እንዲኖረውና በአስፈለገ ጊዜ አገልግሎት ላይ መዋል አለበት::

በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለባችው እንዴት ታውቃላችሁ?

ቤትን እና ቤተሰብን ማመዘጋጀት:

በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት የሚደርሱ ቁስለት ጉዳቶች አብዛኞቹ ከባድ ዕቃ መደርደሪያዎች በመሰበር: በተሰበረ ጠርሙስ: እሳት ቃጠሎ እና ጋዝ ናቸው:: ስለዚህ:
  • የመጻሕፍት የመደርደሪያ: የተሰቀሉ ቴሌቪዥኖችን ዕቃወችን ከግድግዳዎች ማጠናከር
  • የሚከተሉት ዕቃዎች ካሉበት መጥበቃቸውን ያረጋግጡ: የፀሐይ የውሃ ማሞቂያ: የጋዝ ታንኮችና: ማዝጋን::
  • ‭ነዳጅና መርዛማ ነገሮች በተቆለፈና ከሙቀት በራቀ ቦታ ያስቀምጡ
  • ከባድ ነገሮችን አነስተኛ ቦታ ያስቀምጡ
  • ‭ስለ መሬት መንቀጥቀጥ ለቤተሰብን ልምምድ ያድርጉ
  • መሽሎኪያውን: የሃሽማል ማብሪያና ማጥፊያ: የጋዝና ውሃ ቦታወች ለልጆች ያስተምሩ
  • አስተማማኝ የመገባኛ ቦታ ያዘጋጁ

በተገነባ ቦታ ሲሆኑ:

በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት ህንጻ ወይም በትውስጥ ካላችሁ: ወደ ተጠበቀ ቦታ እንደ ቅደም ተከተሉ ሂዱ:
  • ክፍት ነጻ ቦታ- ከተቻለ ክፍትቦታ ውጡ (በተወሰኑ ሰከንድ ውስጥ)
  • የተጠበቀ መጠለያ (ማማድ) ደረጃዎች ስር- ባስቸኳይ መውጣት የማይቻል ከሆነ: ማማድ ውስጥ ግቡ:: ማማድ ከሌለ ደረጃዎች ስር ገብታችሁ የመሬት መንቀጥቀጥ እስኪያበቃ ተቀምጣችሁ ቆዩ: በር አትዝጉ::
  • ከባድ ጠረበዛ ስር ወይንም ውስጣዊ ክፍል ኮርነር-ሁለቱን መመሪያዎች ማሟላት ካልተቻለ: ከባድ ጠረበዛ ስር ወይንም ውስጣዊ ክፍል ኮርነር ተጠለሉ::

በተገነባ ቦታ ለሚገኙ መመሪያ:‬

  • ከውጫዊ ግድግዳና ከመደርደሪያ ራቁ
  • ተምበርክካችሁ ራሳችሁን ተከላከሉ: ወለልተጣብቃችሁ ራሳችሁንና ፊታችሁን ተለላከሉ: ተንቀሳቃሽ ወንበር ላይ ከሆናችሁ: ቆልፉት::
ክፍት ሜዳ ቦታ ላይ ለሚገኙ መመሪያዎች

ክፍት ቦታ - በጣም የተጠበቀ ቦታ!‬

  • ክፍት ቦታ በተቻለ መጠን ከሕንጻዎችና በርቀት መቆየት
  • ‭ከወዳቂ ዕቃዎች ተጠንቀቁ (የግድግዳ ድንጋዮች ማዝጋን የጠርሙስ ስባሪ የኤሌክትሪክ ኬብሎች ወዘተ)
ማወቅ ያስፈልጋል: በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ በመሬት በታች በሚገኙ መጠለያ ሚቅላጥ ውስጥ መቆየት የለም!

መኪና ውስጥ ላሉ መመሪያዎች:

  • ወዲያውኑ መክናውን አቁመው መንቀጥቀጡ እስኪያቋርጥ ድረስ ተሽከርካሪው ውስጥ ይጠብቁ - መኪናው እርስዎን ይከልለወታል!
  • ‬ድልድይ ላይ/ሥር አያቁሙ: ሕንጻዎች አቅራቢያ ወይም ቁልቁለት ላይ አያቁሙ::

ከመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ ትክክለኛ ባህሪ:

  • ‭ማንኛውም ዓይነት እሳት (በሞባይል ስልክ አጠቃቀም ጨምሮ)የጋዝ ፍሳሽ ፍንዳታ ሊያስከትል ስለሚችል::‬
  • ‬ከሕንፃ በመውጣት ክፍት ቦታ ቆዩ ከሕንፃዎች ራቅ በማለት
  • ሕንጻውን ለቃችሁ ከመሄዳችሁ በፊት የጋዝ እና የኤሌክትሪክ ምንጮችን ዝጉ::

የሕንጻውን ጋዝ እና ኤለክትሪክ የሚያድስ ባለ ሙያ ብቻ ነው::

  • የሕንጻው ማሃንዲስ ካልፈቀደ ወደ ተጎዱት ሕንጻዎች መግባት ክልክል ነው (ርዳታ ለማበርከትብቻ ካልሆነ)
  • መረጃ እና መመሪያዎችን ለማግኘት በብዙኃን የመገናኛ አውታሮች አዳምጡ::
  • ተጨማሪ መንቀጥቀጥ ዝግጁ ሁኑ ተጨማሪ መንቀጥቀጥ ከትንሽ ደቂቃዎች አንስቶ እስከ ቀናት ለከሰት ይችላል: በመጀመሪያው መንቀጥቀጥ የተጎዱ ህንጻዎችን ሊያፈር ስይችላል::

ፍርስራሽ ስር ለተያዙ:

  • በአቅራቢያችሁ ፍርስራሽ ስር የተቀበረ ሰው ካለ ባላችህ ዘዴ እና መሳሪያ ተጠቅማችሁ እርዳታ አቅርቡለት: ለምሳሌ በመኪና ማንሻ: በብረትና ቤት ውስጥ በሚገኙ መሳሪያወች::
  • ‬የመጀመሪያ እርዳታ አቅርቡ
  • እናንተ ፍርስራሹ ስር ከሆናችሁ ራሳችሁን ለማዳን ሞክሩ
  • ‭አፍና አፍንጫችሁን በጨርቅ አቧራ እንዳይገባ ሸፍኑ
  • ‭ከደረሳችበት ቧንቧም ሆነ ግድግዳ ያላችሁበት ቦታ እንዲታወቅ በድንጋይ አንኳኩ ወይንም በፊሽካ ንፉ
  • እሳት አታንድዱ

በሚሳይል ጥቃት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እንዴት ታውቃላችሁ?

ከሮኬቶች እና ከሚሳይሎች መከላከል

የሚስማማህን የተጠበቀ መርጠህ የማንቂያ ድምጽ ከተሰማ ጀምሮ መጠለያ ለመግባት 60 ሰከንድ ነው::
  • በማማድ (የቤት መጠለያ) ወይም ማማቅ (የፎቅ መጠለያ) በቶሎው -መጠለያ ግቡ የብረት መስኮትና በር ዝጉ
  • ሚቅላጥ: በጋራ ቤቶች የሚገኝ መጠላየ ሚቅላጥ በደረጃወችአንስቶ መግባት የሚቻል ከሆነ ብቻ: ህዝባዊ ሚቅላጥ በተወሰነው ጊዜ መድረስ የሚቻል ከሆነ ብቻ::
  • የደረጃውን ስር- መጠለያ ክፍል ከሌለ የደረጃውን ስር እንደ መጠለያ መጠቀም ነው 3ኛ ፎቅ ያለው ህንጻ የሚኖሩ ማማድ/ማማቅ/ሚቅላጥ ከሌለው ሁለተኛ ፎቅ ወርደው ደረጃው ስር ይቆዩ 3ኛ ፎቅ ያለው ህንጻ የሚኖሩ ማማድ/ማማቅ/ሚቅላጥ ከሌለው አንድ ፎቅ ወርደው ደረጃው ስር ይቆዩ
  • ወለል ላይ ተቀመጡ (መስኮት መስመር በታች) ውስጣዊ ግድግዳ ዳር መስኮት ፊት ለፊት እንዳይሆን ወይም መታጠቢያ ውስጥ: መጸዳጃ ቤት መምረጥ ይቻላል ቤቶች በግቢያ መገኘት ከሚተኮሱት የሚሳየልና ሮኬት ተፈናጣሪ ሊያጋጥም ስለሚችል አደገኛ ነው:: በድንገተኛ ጊዜ የፎቁንበር ከፍታችሁ ተውት ውጭ ላለ ሰውእንዲሆን::

ከህንጻ/ፎቅ ውጭ

  • በተገነባ አካባቢ- ወደ ቤት/ህንጻ ገብታችሁ መመሪያውን ተከታተሉ
  • በክፍት ቦታ- መሬት ላይ በሆዳችሁ ተኝታችሁ ራሳችሁን በእጃችሁ ሸፍኑ

መኪና ውስጥ ለሚገኙ:

  • በጥንቃቄ መኪናውን በጎዳና ዳርአቁሙ
  • ከመኪና ወጥታችሁ መጠለያ ቦት ግቡ
  • መጠለያ ከሌለ መሬት ላይ በሆዳችሁ ተኝታችሁ ራሳችሁን በእጃችሁ ሸፍኑ

ማወቅ ያስፈልጋል: የፒቁድ ሃኦሬፍ ስልክ ሞቄድ 104
ሌላ መመሪያ ከሌለ ከ10ደቂቃ በኋላ ከመጠለያ መውጣት ይቻላል ከማይታወቁ ቁሳቁሶች መራቅ ይመረጣል:: በአካባቢያችሁ ሮኬት የማይታወቅ ነገር ካያችሁ: ተመልካችን ለቦታ አርቃችሁ ለመከላከያ ሃይል አስተላልፉ::

ቃጠሎ በተነሳ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለባችው እንዴት ያውቃላችሁ?

ቃጠሎ በተነሳ ጊዜ ምን ማድረግ አለ:

  • የእሳት አደጋን በቅድሚያ ጥሩ (102 በሁሉም ስልክ)
  • ባላችሁ መሳሪያ ሁሉእሳቱን ለማጥፋት ሞክሩ (በውሃ: በባልዲ ውሃ: በመወልወያ: በሌላም)
  • ተቀጣጣይ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ከቃጠሎው አካባቢ አርቁ
  • ቤተሰባችሁ በሙሉ ከቦታው መውጣታቸውን አረጋግጡ
  • ለቤተሰባችሁ ለድንገተኛ ጊዜም የመገናኛ ቦታ ወስኑ
  • ቃጠሎው ከአቅማችሁ በላይ ከሆነ ከቦታው ወጥታችሁ ጎረቤትን ፎቁ እንዲለቁ ንገሯቸው
  • ቃጠሎው ተፋፉሞ ጢሱ በዝቶ ከክፍሉ ውጭ አላስወጣችሁ ካለ: ካላችሁበት ሁናችሁ ተጎንበሱ ያለውን መሰኮትና ቀዳዳ ሁሉ ዝጉ (ይህ ዘዴ ጢሱወደ ክፍሉ እንዳይገባ እንዲታገድ ነው)
  • ወደ ውጭ አቅጣጫ የሚከፈት መስኮት ካለ: ወደላይ ወደመስኮቱ የሚጥለቀለቅ ጢስ ከለለ : መስኮቱን ከፍታችሁ ንጹህ አየር አስገቡ: (ወደመስኮቱ የሚዘልቅ ጢስ ካለ መስኮት አይከፈትም)
  • ያላችሁበትን ቦታ ባስቸኳይ ለማሳወቅ ሞክሩ
ወደ ሃሽማልና የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ውሃ መርጨት ክልክል ነው

አደገኛ ፈሳሽ ነገሮች በፈሰሱ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እንዴት ታውቃላችሁ?

በድርጊት ወቅት:

  • ወደ ቤት ገብታችሁ መስኮትንና በርን ዝጉ
  • የማሞቂያ እና የማብሰያ ታኑርን ዝጉ ማዝጋንና ማናፈሻ ቀዳዳወችን: የውሃ ና የጋዝ ቧንቧን በሙሉ ዝጉ
  • ለመጠለያ ክፍል ግቡ: ያለውን በር: መሰኮትና ቀዳዳ ሁሉ ዝጉ: ክፍሉን ማሞቅ እና እሳት ማንደድ ክልክል ነው??
  • ከቤት ውጭ ለሚገኙ- በቶሎው ወደ ተጠበቀ ቦታ ግቡ
  • በመኪና ላይያሉ- ያለውን በር: መሰኮትና ቀዳዳ ሁሉ ማዝጋንም ዝጉ:በመገናኛ ዘዴዎችበሚነገረው መሰረት በጥንቃቄ መንገዳችሁን ቀጥሉ::
  • የአደገኛው ፈሳሽ የህመም ምልክቶች እንደ የራስ ህመም: መጠውለግ: የትንፋሽ እጥረት: ዓይንንእና አፍንጫን ማሳከክ ከተከሰቱ: ተተነካውን አካባቢ በውሃ አጥቦ ለተመልካች ሃኪም ማስተላለፍ ነው::
  • በሜዲያ የሚነገሩትንመመሪያ ተከታተሉ
  • ድርጊቱ ሲከወብ በቱን በአየር ያናፍሱት
የአደገኛ ፈሳሽ ንጥረ ነገሮች በተከሰተ ጊዜ ዋናው አስፈላጊ እርምጃ: አንድ ቦታ መዝጋትና ማዝጋንን ማጥፋት:: ከውጭ ያሉ- ወደ ውስጣዊ ክፍል ይግቡ:: ከውጭ ከመሆን ከውስጥ መሆን ይመረጣል::

መንፈሳዊ ጭንቀት ላደረባቸው የመጀመሪያ እርዳታ ማቅረብ እንዴትአርጋችሁ ታውቃላችሁ?

ለየት ባሉ ሁኔታዎች ከከፍተኛ ውጥረት መቆጠብ ይሻላል::

"አስፈሪ ወይንስ አደገኛ" ብሎ መመርመር: ያላችሁበት ሁኔታ አደገኛ ነው ወይስ ፍርሃት ብቻ? ስጋትን ለማቃለል ከታሰበ እንደሚከተለው ይሆናል:

መሰረታዊ ሰብአዊ ስሜትንና አስፈለጊ ድጋፎችን አበርክቱ

  • ምግብ እና መጠጥ በወቅቱ ተመገቡ (ጣፋጭ ነገሮችንም) በቂ የምኝታ ጊዜ
  • ውስጣዊ ስሜታችሁን ሳትደብቁ ብስጭት: ሳቅ: ለቅሶ: ፍቅርና መከፋትን በጋሃድበ አሳዩ
  • ትንፋሻችሁን በማደራጀት ለመረጋጋት ሞክሩ

ሁኔታውን ሰብሰብ አድርጎ መስመር ማስያዝ

  • በቶሎው ወደ መደበኛ ፕሮግራሞች ለመመለስ ሞክሩ
  • በተቻለ መጠን ቤተሰብን በፕሮግራም አሳትፉ:

እውነተኛና አዲስ መረጃዎችን ፈልጉ

  • እውነተኛ መረጃ ካገኛችሁ በኋላ ለቤተሰብ አማክሩ ለያንዳንዱ እንደ እድሜው
  • ስህተትን ለመበተን ከደህንነት ሃላፊዎች ጋር ግንኙነት አድርጉ (የማህበረሰባዊ ፖሊስ/ የድንገተኛ የሰፈር ሰራተኞች)

የአስፈላጊነትን ስሜት አጠንክሩ

  • ልጆቻችሁ ጎን አትለዩ ስሜታቸውን ያዳብራል
  • ስለድርጊቱ ከቤተሰብ ጋር ተወያዩ
  • የተዋጣችሁበትን መንገድ: በህዮታችሁያሳለፋችሁትንአካፍሉ
  • ከቤተዘመዱ ጋር ግንኙነት መስርቱ

ተሳትፎንና ስራን ደጋግፉ

  • የችሎት ስሜትን ለማሳደግ ቤተሰቦቻችሁን ትንንሽ ምርጫዎችን እንዲያደርጉ ገፋፉ: የምግብ ምርጫ: የልብስ: የስፖርት: ጨዋታ: መደጋገፍ: የጋራ ሽርሽር: ጸሎት መጸለይ::
  • ጊዜ ካላችሁ ድጋፋችሁን ለሌሎች አበርቱ
አዎንታዊ አመለካከት መያዝና ተስፋ አለመቁረጥ አስፈላጊነው ሁኔታ ካልተሻሻለ ከባለሙያ ጋር መማከር ይሻል

አስተውስ! የተለያዩ ሰዎች ለተለያዩ አጋጣሚዎች በተለያዩ መንገዶች ሃሳባቸውን ይገልጻሉ: በድንገተኛ ወቅት የሚሰጡ መልሶችና ሃሳቦች እንደ መደበኛ ጊዜ መታየት አለባቸው::

የፀጥታ ኃይል ድርጅቶች

በእውነተኛ ወቅት ዝግጁና አመች እንዲሆንላችሁ: አስፈላጊ የስልክ ቁጥሮችንና ቅድመ ዝግጅት የሚያስፈልጋቸውን ቁም ነገሮች በዝርዝር አዘጋጅተንላችኋል::

ፍሪጅደር ላይ አጣብቁ